
ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዕቅድ አፈጻጻም የስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ መልዕልት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የአምራች ኢንዲስትሪዎች የማምረት አጠቃቀም 46 በመቶ እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ ንቅናቄው ከተጀመረ ጀምሮ እስከ አሁን በአማካይ የማምረት አቅም ወደ 61 በመቶ ከፍ ብሏል ነው ያሉት።
ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ትኩረት እንዲያገኝ እና የዘርፉ ችግሮች ላይ መፍትሔ ለማስቀመጥ እድል መፍጠሩን ነው የተናገሩት።
ተከታታይነት ያላቸው ውይይቶችን በማድረግ ለችግሮቹ የመፍትሔ ባለቤት መኾን በመቻሉ የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት፣ በራስ ምርት የመኩራትና የመጠቀም ባሕላችን እየተሻሻለ መጥቷል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
