የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራውን በተቀናጀ መንገድ ለመምራት እየተሠራ ነው፡፡

32

ደብረ ብርሃን: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ መርሻ አይሳነው የግብርና ባለሙያዎችን በማሠልጠን እና አርሶ አደሩን ተሳታፊ በማድረግ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራውን በተቀናጀ መንገድ ለመምራት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ሁሉን አቀፍ የምርት ዕድገትን ለማምጣት፣ በምግብ ራስን ለመቻል እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ተፈጥሮን መጠበቅ ተገቢ መኾኑንም ተናግረዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በመላው ዓለም ለተፈጥሮ ሀብት ትኩረት ባለመስጠቱ ዋጋ ማስከፈሉን ገልጸዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ስር በሚገኙ በ13 የገጠር ቀበሌዎች የሚከወነውን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ በትኩረት መሥራት ይገባልም ብለዋል። የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን ውጤታማ ለማድረግ መሪዎች እና ባለሙያዎች በትኩረት እንዲሠሩም አሳስበዋል።

በከተማ አሥተዳደሩ በነባር 599 እና በአዲስ ደግሞ 846 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ይከወናል ነው የተባለው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ የመሬታቸውን ለምነት እየመለሰ መኾኑን የባንጃ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
Next articleየሰቆጣ ቃልኪዳን ለውጥ ያሳየ ፕሮግራም መኾኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ።