የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ላይ እየተመከረ ነው።

49

ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ”የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ለዘላቂ ምርታማነት ዕድገት” በሚል መሪ መልዕክት ለምዕራብ አማራ የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማኅበረሰብ ተፋሰስ ልማት ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልል ግብርና ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት፣ የዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ እና የቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በሚሠሩት የተቀናጁ የተፋሰስ ልማት አቅጣጫዎች፣ ሊያጋጥሙ በሚችሉ እንቅፋቶች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የጸጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ።
Next article“ከተማችን የጋራ ቤታችን ናት” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው