
ባሕርዳር: ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጸጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የኾነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን በሰላም መጠናቀቁን ነው ለመገናኛ ብዙኃን በላከዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው። በተመሳሳይ ዛሬ የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ገልጿል።
በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት፣ ለበዓሉ አስተባባሪዎች፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የጸጥታ ተቋማት አመራር እና አባላት የጸጥታ ደኅንነት ጥምር ኃይል ምስጋና ማቅረቡን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!