ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ ያሉ በዓላት በሰላም መጠናቀቃቸውን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

39

ባሕርዳር: ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ባወጣው የምስጋና መልዕክት ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ ያሉ በዓላት በዓደባባይ በድምቀት የሚከበሩ በዓላት መኾናቸውን ገልጿል።

በየጊዜው ድምቀታቸው የበርካቶችን ቀልብ እየሳበ መኾኑንም አመላክቷል። የዘንድሮው የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓል በሰላም እጅግ ባመረ ሁናቴ በድምቀት ተከብሯል ነው ያለው።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከዋዜማው አንስቶ ያለመታከት የተሰጣቸውን ስምሪት ለሸፈኑ የጸጥታ ኀይሎች ፖሊስ ኮሚሽኑ ምስጋናውን ያቀርባል ብሏል በመልዕክቱ።

ፖሊስ የሃይማኖት አባቶች፣ወጣቶች እና እኩይ ዓላማ ባላቸው አካላት በዓሉን ለማደናቀፍ ታቅደው የነበሩ ሴራዎችን እንዲከሽፍ የመረጃ ምንጭ ለነበራችሁ ምስጋና ያቀርባል ነው ያለው። ሰላማዊ በዓል እንዲከበር ለተባበራች ሁሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ ምስጋናውን ያቀርባል ብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በጎንደር ከውጭ ሀገር ጎብኝዎች ጋር መገናኘታቸውን ገለጹ።
Next articleጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የጸጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ።