
ባሕርዳር: ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በጎንደር የጥምቀት በዓልን የታደሙ የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በዓሉን በድምቀት የሚያከብሩ የውጭ የሀገር ጎብኝዎችን ማግኘት እና መቀበል አስደሳች ነበር ብለዋል።
የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በዓሉ ወደር የለሽ መኾኑን እና በሕይወት አጋጣሚ ውስጥ እንድ ጊዜ የሚያገኙት እንደኾነ እንደነገሯቸውም ገልጸዋል። የጥምቀት አይነት በዓላት የኢትዮጵያን ታሪካዊ እና ባሕል እሴቶች የበለጠ እንደሚያበለጽጉም ፕሬዚዳንቱ አስፍረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!