የቃና ዘገሊላ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

29

ባሕርዳር : ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቃና ዘገሊላ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በድምቀት እየተከበረ ነው።

ከደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የቃና ዘገሊላ ዓመታዊ ክብረ በዓል በዋሻው ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።

ቃና ዘገሊላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንደኛው ነው። ቃና ዘገሊላ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባሻገር ባሕላዊ ክዋኔዎች የሚፈጸሙበት፣ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ከፍ የሚያደርግ ደማቅ በዓል ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለአዕምሮ ሕሙማን በጤና ተቋማት ከሚሰጠው ሕክምና ባለፈ የማኅበረሰቡ እንክብካቤ ያስፈልጋል” የሥነ አዕምሮ ባለሙያ
Next articleየሕዝብ ችግሮች በየደረጃው ባለው የመንግሥት መዋቅር እንዲፈቱ ይሠራል።