“ጥምቀት ፍቅር፣ ትህትና እና ሰላም የተሰበከበት ታላቅ በዓል ነው” ዲያቆን ሸጋው ውቤ

61

ደባርቅ: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በተለያዩ መንፈሳዊ እና ባሕላዊ ክዋኔዎች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ ከመንፈሳዊ ይዘቱ በዘለለ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ የወል እሴቶችን ቀጣይነት በማረጋገጥ በኩል ጠቀሜታው የጎላ ነው።

የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ተወካይ ሥራ አስኪያጅ እና ዋና ጸሐፊ መልዓከ ኀይል አስምሮ ዋካ ጥምቀት የተሰወረው የተገለጠበት፣ የጠፋው የተገኘበት፣ ምስጢር የተበሰረበት በዓል ነው ብለዋል።

“ጥምቀት ፍቅር፣ ትህትና እና ሰላም የተሰበከበት ታላቅ በዓል ነው” ያሉት ደግሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ ናቸው። የጥምቀት በዓልን ስናስብ የክርስቶስን ፍቅር በማጤን፣ እርስ በእርስ በመደማመጥ እና በመከባበር ሊሆን ይገባል” ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዓሉን ስናከብር ከመነቃቀፍ ይልቅ በመተቃቀፍ ከመለያየት ይልቅ በአንድነት ሊኾን ይገባል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት
Next articleቃና ዘገሊላ ውኃ ወደ ወይን የተቀየረበት።