“በዓሉን ስናከብር ከመነቃቀፍ ይልቅ በመተቃቀፍ ከመለያየት ይልቅ በአንድነት ሊኾን ይገባል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት

31

ደብረ ብርሃን: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በታሪክ አምባዋ በደብረብርሃን ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። የጥምቀት በዓል የተከበረው ከተማ አሥተዳደሩ በሰጠው አዲሱ ቡሌ ወርቄ ዓደባባይ ነው። በዓሉ በዚህ አደባባይ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የጥምቀት በአል በአዲሱ ቦታ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር ከመነቃቀፍ ይልቅ በመተቃቀፍ ከመለያየት ይልቅ በአንድነት ሊኾን ይገባል ነው ያሉት። ያጋጠሙንን ፈተናዎች ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መሥራት ይገባናልም ብለዋል። በዓለም አቀፍ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል ለከተማችን ቱሩዝም መዳረሻ ትልቅ ፀጋን ይዞ ይመጣል ነው ያሉት።

ጥምቀት በደብረብርሃን በአዲሱ ቦታ መከበሩ እና ለሕዝቡ የነበረው የቦታ ጥበት በመቅረፉ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛልም ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ትሕትና የልዕልና መሠረት ነው” መጋቢ ሀዲስ መምህር ዜናዊ አሸተ
Next article“ጥምቀት ፍቅር፣ ትህትና እና ሰላም የተሰበከበት ታላቅ በዓል ነው” ዲያቆን ሸጋው ውቤ