“ሁላችንም ለሀገር ሰላም እና ዕድገት የሚጠበቅብንን ልንወጣ ይገባል” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

45

ሁላችንም ለሀገር ሰላም እና ዕድገት የሚጠበቅብንን ልንወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ፡፡
ፓትርያርኩ ሁሉም ሰው ስለ ሰላም ዋጋ ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የሰው ልጅ ዘላቂ ሕይወትን መቀዳጀት የሚችለው መልካም ሰብዕና ሲላበስ እና ፈጣሪውን ሲፈራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ ለሀገር ሰላም እና ዕድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመተሳሰብ እና በአብሮነት ለመቅረፍ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ ከምታከብራቸው ሃይማኖቶታዊ በዓላት መካከል ጥምቀት አንዱ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው።
Next article“ትሕትና የልዕልና መሠረት ነው” መጋቢ ሀዲስ መምህር ዜናዊ አሸተ