“የጥምቀት በዓልን ስናከብር ፍቅርን፣ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መትጋትን በተግባር በማሳየት መኾን አለበት” ብፁዕ አቡነ በርቶሎሚዎስ

26

ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በደመቀ ሥነ-ሥርዓት በድሬዳዋ እየተከበረ ነው።

በድሬዳዋ እየተከበረ ባለው በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርቶሎሚዎስ፣ ሊቃውንት እና ምዕምናን ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርቶሎሚዎስ የጥምቀት በዓልን ስናከብር ፍቅርን እና ቸርነትን ለሰዎች በመለገስ መኾን እንዳለበት ገልጸዋል። የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ማለትን እና በትህትና ለሌሎች የመታዘዝን አስፈላጊነት ያስተማረበት ተምሳሌት ነው ብለዋል።

እኛም የጥምቀት በዓልን ስናከብር መታዘዝን፣ የእርስ በእርስ ፍቅርን፣ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መትጋትን በተግባር በማሳየት መኾን አለበት ነው ያሉት።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አሥተዳደር የካቢኔ ጉዳዮች እና የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ገበየሁ ጥላሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ ፍቅር እና አንድነትን በማጽናት ሊኾን ይገባል ብለዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተባበር እንዲኾንም መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጥምቀት ሁላችንም በፍቅር እና በትህትና እንድንኖር ያስተምራል” አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ
Next articleየጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው።