
ደብረ ማርቆስ፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ በደብረ ማርቆስ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው ካደሩበት የባሕረ ጥምቀቱ ስፍራ የቤተክርስቲያኗ ሊቃውንት ቅዳሴ፣ ማህሌት እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ሲያከናውኑ አድረዋል፣ አርፍደዋልም።
የጥምቀት ሥርዓተ ክዋኔውም የምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዲዮናሲዮስ ተባርኮ ተከናውኗል።
ታቦታቱ ከሥርዓተ ጥምቀቱ ክዋኔ በኋላ ወደ መንበረ ክብራቸው በዕምነቱ ተከታዮች በዝማሬ እልልታ ታጅበው እየተመለሱም ይገኛሉ።
አሚኮ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች ጥምቀት አንድነትን እና ትህትናን በተግባር የተማርንበት በመኾኑ እኛም ለሰው ልጆች ሰላም እና አብሮነት ልንሠራ ይገባል ብለዋል።
ጥምቀቱ በአንድነት እና በፍቅር እንዳሠባሠበን ሁሉ ጥልን በእርቅ እና በይቅርታ በመለወጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ተምረን ለሀገራችን ሰላም መኾን የድርሻችን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!