
ፍኖተ ሰላም፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በፍኖተ ሰላም ከተማ ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በጥምቀት በዓሉ ላይ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ወርዶ ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ ‘ እኔ አገልጋይ ባሪያህ ነኝ እንጅ እንዴት አንተን ላጠምቅ እችላለሁ አለ’ በሚል ርዕስ ላይ ተነስተው ለአማኞቹ አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
ብጹዕነታቸው በምስጢረ ጥምቀቱ የተገለጠው ነገርን ሁሉ በትህትና ማድረግ እንደሚገባን ነው ብለዋል።
ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ትህትናን እንዳስተማረ እኛም ጥያቄያችን ወደ እግዚአብሔር በትህትና ልናቀርብ ይገባልም ነው ያሉት።
አሁን ላይም በባሕረ ጥምቀቱ ላይ ያደሩ ታቦታት በአማኞች እና በበዓሉ ታዳሚያን ታጅበው በሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ሥርአቶች ወደ መንበረ ክብራቸው እየተመለሱም ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!