” ጥምቀት ለኢትዮጵያዊያን ትልቁ መገለጫችን ነው” የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲባ ደሴ መኮንን

32

ደብረ ታቦር: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በደብረ ታቦር ከተማ አጅባር ሜዳ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን፣ ሊቃውንት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ምዕምናን ተገኝተዋል።

በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ጥምቀት ለኢትዮጵያዊያን ትልቁ መገለጫችን ነው ብለዋል። የጥምቀት በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት እንደሚከበርም ገልጸዋል።

ጥምቀት ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ ባለፈ ብዙ ባሕላዊ ክዋኔዎች የሚተገበሩበት በዓል መኾኑንም አንስተዋል።

የጥር ወር በአጅባር ታላላቅ ሃይማኖታዊ በዓላትን የምናከብርበት ወቅት ነው ያሉት ከንቲባው አጅባር ከጥር 10 ጀምሮ እስከ ጥር 29 ድረስ በርካታ በዓላት ይከበሩበታል ነው ያሉት።

ሁሉንም በዓላት በቀደመ የመከባበር ባሕላችን መሠረት በሰላም በማክበር የምንታወቅበትን ተግባር መከወን ይገባናልም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተላከ መልዕክት ለዩጋንዳ እና ለኬኒያ ፕሬዚዳንቶች አደረሱ።
Next articleየጥምቀት በዓል በኮምቦልቻ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።