“ትህትና እና ይቅር ባይነት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰበካቸው የሰው ልጅ መሠረቶች ናቸው” መጋቢ ምስጢር ዘረዳዊት አለባቸው

37

እንጅባራ: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ዘንድ በየ ዓመቱ በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ዕለቱን በተመለከተ ወንጌል የሰበኩት የአዊ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሥስጢር ዘረዳዊት አለባቸው ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ ዝቅ ብሎ በመጠመቅ ለሰው ልጆች ትህትናን ያስተማረበት፣

የሰው ልጆች ከዲያቢሎስ ባርነት ነፃ የወጡበት ታላቅ የድኅነት በዓል ነው ብለዋል። “ትህትና እና ይቅር ባይነት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ሳለ በተግባር የሰበካቸው የሰው ልጅ የኑሮ መሠረቶች እንደኾኑም ሥራ አስኪያጁ በትምህርታቸው አንስተዋል።

በበዓሉ የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ ለሃይማኖቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በመልዕክታቸው

ትውልዱ የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮን ወደ ተግባር በመቀየር ፈጣሪን የሚያስደስት እና ለሕዝብ እና ለሀገር የሚጠቅም ሥራ የመሥራት ታሪካዊ አደራ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የከተራ እና የጥምቀት በዓት አምረው እና ደምቀው እንዲከበሩ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችም የከተራ እና የጥምቀት በዓላት እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቀው በድምቀት ማክበራቸው እንዳስደሰታቸውም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጥምቀት በዓል በሁመራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
Next articleየጥምቀት በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።