በሐረሪ ክልል የጥምቀት በዓል በደመቀ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡

10

ባሕር ዳር: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር: ጥር 11/2017(አሚኮ) በዓሉ ክርስቶስ ያሳየውን ፍቅር እና ትህትና በመላበስ አብሮነትን ማጠናከር ይገባል ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ገልጸዋል።

በባህረ-ጥምቀቱ ላይ ለምዕመናን መልዕክት ያስተላለፉት እና ትምህርት የሰጡት የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ እንደተናገሩት በዓሉ የማኝነት ምስጢር የተገለጸበት ነው።

ምዕመናኑም ክርስቶስ ያሳየውን ፍቅር እና ትህትናን በመላበስ አብሮነትን ማጠናከር ይገባዋል ብለዋል በመልዕክታቸው።

በተለይም ልዩነቶችን በማስወገድና ይቅርታን እና ምህረትን በማስቀደም አንድነትን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዓሉ ሲከበር አቅመ ደካሞችን እና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እና በመደገፍ መኾን እንዳለበትም ነው መልዕክት ያስተላለፉል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጥምቀት ለሰው ልጆች አንድነትን ያጎናጸፈ የአብሮነት በዓል ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት እሸቱ
Next articleየጥምቀት በዓል በሁመራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።