
ሰቆጣ፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰቆጣ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
በሥርዓተ ጥምቀቱ ተገኝተው መልዕክት ያሥተላለፉት የሰቆጣ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጌትነት እሸቱ የጥምቀት በዓል ለሰው ልጆች አንድነትን እና አብሮነትን ያጎናጸፈ በዓል መኾኑን ገልጸዋል።
የነጻነት ተምሳሌት የኾነው የጥምቀት በዓል ሲከበር የጥላቻ ጭጋግን በማስወገድ የፍቅር ካባን ደርቦ ማክበር ይገባል ነው ያሉት።
በመደጋገፍ እና በመረዳዳት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ጌትነት በአካባቢያቸው ያለውን አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለመለወጥ በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።
የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ የተራቡትን በማብላት፣ የተራቆቱትን በማልበስ በዓሉን እያከበሩ ክርስቶስን በተግባር መምሰል እንደሚገባም ገልጸዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በከተማዋ ያሉ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን ማክበር እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
ለጥምቀት በዓልም የእንኳን አደረሳችሁና መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
