
ባሕር ዳር: ጥር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በውቡ የጣና ሐይቅ ዳርቻ በሚገኘውን ጥምቀተ ባሕር ሥርዓተ ጥምቀቱ በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ አብርሃም ተገኝተው አማኞችን እየባረኩ ነው። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ከንጋቱ ጀምሮ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
ብጹዕ አቡነ አብርሃም ጥምቀተ ባሕሩን ከባረኩ በኃላ ካሕናት አማኞችን እየጸበሉ ነው።
አማኞች አሁንም ድረስ ወደ ቦታው በመምጣት የሥርዓተ ጥምቀቱ ተካፋይ እየኾኑ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!