
አዳማ ፡ ጥር 11/2017 ዓ.ም { አሚኮ} የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚከበር ደማቅ የዓደባባይ በዓል ነው።
ዛሬ እየተከወነ የሚገኘዉ የጥምቀት ሥርዓትም በአዳማ ከተማ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎሪዮስ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።
አሚኮ የጥምቀት በዓልን ሥነ ሥርዓት ከኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ እያደረሰ ነው። አሁን ላይ ሥርዓተ ጥምቀቱ እየተካሄደ ነው::
ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ-ከአዳማ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!