“የጎንደር የተሐድሶ ዘመን ዛሬ ነው” ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

29

ባሕር ዳር: ጥር 11/2017 ዓ.ም(አማኮ) የጥምቀት ክብረ በዓል በጎንደር በድምቀት እየተከበረ ነው። በጥምቀተ ባሕሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ የጥምቀተ ባሕር ላይ ታድሜ የነበርኩት የዛሬ 50 ዓመት ነበር ብለው አስታውሰዋል። የዚህ የጥምቀት በዓል በጎንደር ትውስታው ደማቅ ነበር ነው ያሉት።

በዚህ ዓመት የጥምቀት በዓል እንዲህ እንዲደምቅ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል። ጎንደር ትናንትም ዛሬም የጥበብ ሀገር እንደኾነች ገልጸዋል።

“የጎንደር የመልሶ እና የተሐድሶ ዘመን ዛሬ ነውም” ብለዋል። ይህ ትውልድ ጎንደርን መጠበቅ ብቻ ሳይኾን ማሸጋገርም ይጠበቅበታል ነው ያሉት። ይህ ዕድል ለዚህ ዘመን ትውልድ ሊያመልጠው አይገባም ብለዋል።

ለዚህ ሁሉ መሠረቱ ግን ሰላም ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ሰላም የሌለው ማኅበረሰብ ምንም እንዳልኾነ ተናግረዋል። ለሰላም የማያገባው ሊኖርም አይችልም እና ሁሉም ለሰላም መረጋገጥ የራሱን ጠጠር መወርወር እንዳለበት አሳስበዋል።

ሰላም ከተረጋገጠ ጎንደር ከዚህ በላይ ትደምቃለች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ። ለዚህ ደግሞ ለማገዝ ዝግጁዎች ነን ብለዋል።

በመጨረሻም በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኀላፊነታችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጥርን ናፍቀን፣ በጥር ደግሰን፣ በጥር የምናምር የመናገሻዋ ከተማ ነዋሪዎች ነን” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው
Next article“የጥምቀት በዓል ከመሠረቱ የሰላም ነጋሪት የታወጀበት፣ የፍቅር እምቢልታ የተነፋበት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ