
ባሕርዳር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የከተራ በዓል በቅዱስ ላሊበላ በድምቀት እየተከበረ ነው። ላሊበላ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በድምቀት ከሚከበሩቸው አካባቢዎች መካከል አንደኛዋ ናት።
የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ላሊበላ ጥምቀትንም በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ታከብራለች።
በከተራ በዓል ሥነ ሥርዓቱ የውጭ ሀገር እንግዶች በብዛት ታድመዋል። ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በታላቅ አጀብ ጥምቀተ ባሕር ደርሰዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!