
ገንዳ ውኃ: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ሰላማ እንዳሉት የጥምቀት በዓል ዮሐንስ ወደ ፈጣሪው መምጣት ሲገባው ፈጣሪው ወደ ዮሐንስ በመምጣቱ ትህትናን ያስተማረበት የትኅትና በዓል ነው።
በዓሉ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት የሰጠበት ስለመኾኑ አብራርተዋል። ብጹዕነታቸው በሀገሪቱ ላይ እየታየ ያለው ችግር እንዲወገድ ሁሉም ወደ ፈጣሪ መጸለይ ያስፈልጋል ነው ያሉት። አማኙ በዓሉን ሲያከብር ያለው ለሌለው በመስጠት እና በመደጋገፍ ሊኾን እንደሚገባም ተናገረዋል። አማኙ በዓሉን ሲያከብር የጥላቻን ግድግዳ በማፍረስ እና ሰላምን በመስበክ እንዲኾንም አስገንዝበዋል።
አሚኮ ያነጋገረው የበዓሉ አስተባባሪ ወጣት አፈወርቅ ነጋሽ በዓሉ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ወጣቶች የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን በሰላም እንዲከበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የበዓሉ ተሳታፊ ወይዘሮ አዳነች ታደሠ በዓሉ በከተማው በድምቀት መጀመሩን ተናግረው በቀጣይ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ማንኛውም አካል ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!