በሰቆጣ ከተማ የከተራ በዓል ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባሕሩ እየወረዱ ነው።

20

ሰቆጣ: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ የከተራ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓትና ድምቀቱን ጠብቆ እየተከበረ ነው። ታቦታቱ ከየአድባራቱ ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕሩ እየወረዱ ይገኛሉ።

ታቦታቱንም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ በገና ደርዳሪዎች እና የእምነቱ ተከታዮች በመዝሙር እና በእልልታ አጅበው እየሸኟቸው ነው።

የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ ሕዝበ ክርስትያኑን እየባረኩ ይገኛሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጅማ ከተማ የከተራ በዓል እየተከበረ ነው
Next article“ጥምቀት ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው የአደባባይ የወል በዓል ነው” የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት