
አዲስ አበባ: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የከተራ እና ጥምቀት በዓላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሥ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚከበሩ ደማቅ የአደባባይ በዓላት ናቸው። ዛሬ የሚካሄደው የከተራ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች ደምቆ እየተከናወነ ነው።
አሚኮ የከተራ እና ጥምቀት በዓላትን ለተከታታዮቹ ለማድረስ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ተገኝቷል። በአዳማ ከተማ የከተራ በዓል በድምቀት እየተካሄደ ነው። አሁን ላይ ታቦታት በቀሳውስቱ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እና በእምነቱ ተከታዮች እልልታ ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባሕር በድምቀት በመውረድ ላይ ይገኛሉ።
ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ ከአዳማ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!