በደሴ ከተማ ታቦታት ወደ ባሕረ ጥምቀት እየወረዱ ነው።

22

ደሴ: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ ታቦታት ከየአድባራቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው በደማቅ እጀባ ወደ ባሕረ ጥምቀት እየወረዱ ነው።

በደሴ ከተማ ከየአድባራቱ ታቦታት በምዕመናን ታጅበው በተለምዶ ሆጤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ማደሪያቸው እያመሩ ነው። ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሠንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መዘምራን በዝማሬ፣ ምዕምናን ደግሞ በእልልታ እና በኾታ ታቦታቱን እያጀቡ በመጓዝ ላይ ናቸው።

ዘጋቢ:- ደምስ አረጋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረ ማርቆስ ታቦታት ወደ ባሕረ ጥምቀት እየወረዱ ነው።
Next articleየከተራ በዓል በወልድያ ከተማ እየተከበረ ነው።