
ባሕር ዳር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ታቦታት ከመንበራቸው በካህናት እና ዲያቆናት ወረብ እና ሽብሸባ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ዝማሬ፣ በምዕመናን እልልታ እና ሆታ ታጅበው ከባሕረ ጥምቀቱ ደርሰዋል።
በሥነ ሥርዓቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተገኝተዋል።
የከተራ ሥነ ሥርዓቱ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እየተከበረ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!