
ባሕር ዳር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ታቦታት ከየአድባራቱ ወጥተው ወደማደሪያቸው እያመሩ ነው።
ታቦታቱ የሚወርዱት በታላቁ የዓባይ ወንዝ ዳርቻ ነው። ነገ የሚካሄደው ሥርዓተ ጥምቀትም በዚሁ ይካሄዳል። ካህናት፣ ዲያቆናት እና መዘምራን በዝማሬ፣ የእምነቱ ተከታዮች ደግሞ በእልልታ እና በኾታ ታቦታቱን እያጀቡ በመጓዝ ላይ ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!