በባሕርዳር ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባሕር እየወረዱ ነው።

20

ባሕር ዳር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር የጥምቀት በዓል ዋዜማ የከተራ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

የአድባራት እና የገዳማት ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው የጣና ሐይቅ ዳርቻ ባሕረ ጥምቀት እያመሩ ነው።

ታቦታቱ በካህናቱ እና ሊቃውንት ወረብና ሽብሻቦ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መዝሙር፣ በምዕመናን እልልታ እና ሆታ ታጅበው ነው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እያመሩ የሚገኙት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዓሉ የሰላም፣ የምህረት፣ የፍቅርና የበረከት ይሁንልን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleእንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሣችሁ! አደረሰን!