
ሁመራ: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሁመራ ከተማ ወጣቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ታቦታቱ ወደ ከተራ ቦታው የሚያልፉባቸውን መንገዶች አጥበዋል።
የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሥነ ሥርዓቱ የሚከናወነው በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ነው። በመኾኑም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች፤ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች፣ ከልዩ ልዩ የጸጥታ መዋቅር የመጡ አባላት የታቦታቱን ማለፊያ አስፋልት መንገዶች ሲያጥቡ አርፍደዋል።
አሚኮ በአስፋልት አጠባው ላይ ሲሳተፉ ያገኛቸው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ አቶ ዳውድ በሽር “ተከባብሮ አብሮ መኖር ደስ ይላል” ብለዋል።
አቶ ዳውድ አክለውም “ለመላው የእምነቱ ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ” ብለዋል።
የከተራ ሥነ ሥርዓቱም ከ10 ሠዓት ጀምሮ እንደሚጀመር ታውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን