የባለዘንባባዋ ከተማ ልጆች ጎዳናዎችን በማጽዳት ለከተራ እና ጥምቀት በዓል እያዘጋጁ ነው።

26

ባሕር ዳር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ባለዘንባባዋ ከተማ ባሕር ዳር ለወትሮውም ጽዱ እና ማራኪ ናት። ዛሬ በድምቀት ለሚከበረው የከተራ በዓል እና ለነገውም የጥምቀት በዓል ጎዳናዎቿን በውኃ እና በሳሙና የበለጠ የማጽዳት መርሐ ግብር ከጠዋት ጀምሮ እየተካሄደ ነው።

በጽዳት እና የአስፋልት መንገዶችን የማጠብ መርሐ ግብሩ ላይ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተው ከከተማዋ ወጣቶች ጋር እየተሳተፋ ነው ።

የከተማዋ የጽዳት እና ውበት ባለሙያዎች ከወጣቶች እና ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር ነው ጎዳናዎችን እያጸዱ ለበዓላቱ እያዘጋጁ የሚገኙት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ጎንደር ከተማ ገቡ።
Next articleከተራ ምን ማለት ነው?