ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ጎንደር ከተማ ገቡ።

31

ጎንደር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና ልዑካቸው በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደን ጨምሮ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች ናቸው ጎንደር ከተማ የተገኙት።

ርእሰ መሥተዳደሩ እና ልዑካቸው ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘውን ጨምሮ ከፍተኛ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጎንደር ከተማ ገቡ።
Next articleየባለዘንባባዋ ከተማ ልጆች ጎዳናዎችን በማጽዳት ለከተራ እና ጥምቀት በዓል እያዘጋጁ ነው።