
ጎንደር: ጥር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱና አፈጉባኤው ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!