የጎንደር እርግብ በር መስጊድ ዕድሳት እየተደረገለት ነው።

29

ባሕር ዳር: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የሚገኘው እርግብ በር መስጊድ በከተማ አሥተዳደሩ እና በኅብረተሰቡ እድሳት እየተደረገለት ነው። በምክትል ርዕሠ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ አሥተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳኝ ጣሰው ጎንደር የምትታወቀው በተለያዩ የእምነት ተከታዮች አብሮነት እና መተሳሰብ ነው ብለዋል።

ጎንደር አንዱ ከአንዱ ተከባብሮ እና ተረዳድቶ የሚኖሩባት ከተማ ናት ያሉት ኀላፊው የነበሩ የአብሮነት እሴቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል። የሃይማኖት አባቶች ለአንድነት በመቆም የተጀመሩ የከተማዋ ልማቶችን በማስቀጠል በኩል ከከተማ አሥተዳደሩ ጎን እንዲኾኑም አሳስበዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ጎንደር በታሪኳ በሃይማኖት አባቶች ማኅበራዊ መስተጋብር፣ በፍቅር እና በአንድነት የምትታወቅ መኾኗን ገልጸዋል። እየታደሰ ያለው የእርግብ በር መስጊድ የመተባበር እና በአንድ የመቆም ተምሳሌት ነውም ብለዋል። የእኛ ዘመን የሃይማኖት አባቶች ለአንድነት፣ ለሰላም እና ለመተጋገዝ ትልቅ ድርሻ አላቸው ነው ያሉት።በአብሮነት መርህ ላይ እንድንቆም ላደረጉ የሃይማኖት አባቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የጎንደር ከተማ የእስልምና ምክር ቤት ለዕድሳት ሥራው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተቋማት የሥራ ኀላፊዎች ዕውቅና እና ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያዊ ኅብር በጎንደር ሰማይ ስር”
Next article” ጎንደር ሦስት ነገሮች ተሸምነው የሠሯት ከተማ ናት፣ እምነት፣ መንግሥት እና ኅብረ ብሔራዊነት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ