
ደባርቅ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከጸጥታ ኃይሉ የቁጥጥር እና የጥበቃ ሥራ በተጨማሪ ማኅበረሰቡ ንቁ ተሳታፊ ሊኾን እንደሚገባም አሳስቧል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ሚዲያና ኮምኒኬሽን ዋና ክፍል ኀላፊ ኮማንደር በሬ ተሻገር በበዓሉ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል ተግባራትን ለመከላከል የጸጥታ ኃይሉ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ስምሪት ወስዷል ብለዋል።
ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመሰለፍ ራሱን እንዲጠብቅና በዓሉ በሰላም እንዲከበር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም አሳስበዋል።
ምዕመናን፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከጸጥታ መዋቅሩ የሚሰጡ መመሪያዎችን በቀናነት ተቀብሎ በመተግበር የተለመደ መልካም ትብብራቸውን እንዲፈጽሙም አስገንዝበዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልም የእንኳን እረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!