
አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በተያዘዉ የበጋ ወራት የምርት ብክነትን ለመከላከል በሰብል መሠብሠቢያ ቴክኖሎጂ ሰብል እንዲሰበሰብ ተደርጓል ነው ያሉት።
በዚህም እንደ ሀገር በዘር ከተሸፈነው 29 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ውስጥ በ18 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን ሰብል መሰብሰብ መቻሉን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ስንዴ፣ ጤፍ፣ ሩዝ እና ሌሎች ምርቶችን በተገቢዉ መንገድ መሠብሠብ መቻሉንም ነዉ የተናገሩት።
ወቅቱ የበጋ መስኖ የሚከወንበት በመኾኑ ተገቢዉን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በበጋ መስኖ አርሶ አደሮች ተገቢዉን ምርት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸዉን ጠቅሰዋል። በበጋ መስኖ ኢትዮጵያ ከስንዴ ምርት የምታገኘዉን ገቢ ለማሳደግም ይሠራል ነዉ ያሉት።
መንግሥት የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን እያከናወነ ነው፤ በ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን መሬት ላይ የተፋሰስ ልማቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል ሲሉም ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!