“መንግሥት ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ ነው” ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)

38

አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን ሢሠራ መቆየቱን ገልጸዋል። የሰላም ኮሚቴዎችን በየአካባቢው በማቋቋም ሰላም ለማስፈን መሠራቱን ጠቅሰዋል።

ነፍጥ ያነሱ ኀይሎች ለንግግር በር እንዲከፍቱ በመደረጉ የታጠቁ ኀይሎች ወደ ንግግር እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ልዩነቶችን በውይይቶች ለማጥበብ እና ለመፍታት መንግሥት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል የታጠቁ ኀይሎችም ለውይይት ቅድሚያ ሰጥተው ወደ ተሃድሶ ማዕከል እየገቡ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በተሠራው ሰላምን የማስፈን ሥራ ለውጦች መምጣታቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

መንግሥት አሁንም የሰላም አማራጭን መከተል ላይ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ተግባራዊ ባደረገችዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ተኪ ምርትን ማበረታታት ተችሏል”የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleከ18 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ሰብል ተሠብሥቧል።