“ኢትዮጵያ ተግባራዊ ባደረገችዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ተኪ ምርትን ማበረታታት ተችሏል”የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

18

አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ ሀገር ተግባራዊ የተደረገዉ ማክሮ “ኢትዮጵያ ተግባራዊ ባደረገችዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ተኪ ምርትን ማበረታታት ተችሏል”የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዲስ አበባ: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ ሀገር ተግባራዊ የተደረገዉ ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ የሀገር ዉስጥ ምርትን የደገፈ የጥሬ እቃ አቅርቦት እንዲኖር ያስቻለ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ ተናግረዋል።

ይህ ማሻሻያ አቅርቦት በበቂ ኹኔታ እንዲኖር በማድረግ ኢንዲስቱሪዎች ምርት በተገቢዉ ኹኔታ እንዲያመርቱ የሚያስችል ነዉ ብለዋል። መንግሥት ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻሉን ተከትሎ የዋጋ ንረት እንዳይኖር መሰረታዊ ምርቶች ላይ ተገቢዉን ድጎማና ቁጥጥር በማድረግ ለማኅበረሰቡ ምርትን እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ማሻሻያዉ የዉጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲኖር ከማድረጉ በተጨማሪ የዋጋ ንረትን ማረጋጋት ያስቻለ ነዉም ነዉ ያሉት። ማሻሻያዉ ተግባራዊ መደረጉ የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር አድርጎታልም ነዉ ያሉት።

የዚሁ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል የሆነዉ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ተግባራ መደረጉ የባንኮች የማበደር አቅም እንዲጨምር በማድረግ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የሚያስችል ነዉም ሲሉ አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጥምቀትን በጎንደር የባሕል ሳምንት ማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
Next article“መንግሥት ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ ነው” ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)