ጥምቀትን በጎንደር የባሕል ሳምንት ማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

49

ጎንደር: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 15ኛው ጥምቀትን በጎንደር የባሕል ሳምንት ማጠቃለያ መርሐ ግብር እና 16ኛው የአማራ ክልል ባሕል እና ኪነ-ጥበብ ፌስቲባል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የጎንደር ከተማ ክፍለ ከተሞች የባሕል ቡድኖች እና የተወዳዳሪ ዞኖች ልዑካን ቡድኖች የባሕል እና እሴት መገለጫዎቻቸውን ለታዳሚያን አስተዋውቀዋል።

ከከሰዓት በኋላ በሚኖረው የማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትሯን ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ጎንደር ገቡ።
Next article“ኢትዮጵያ ተግባራዊ ባደረገችዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ተኪ ምርትን ማበረታታት ተችሏል”የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት