
ባሕር ዳር: 09/2017ዓ.ም (አሚኮ) የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ጎንደር ከተማ ገብተዋል። የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጎንደር ከተማ የተገኙት በከተማዋ እየተካሄደ በሚገኘው በ16 ኛው ክልል ዓቀፍ የባሕል ፌስቲባል የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ለመታደም ነው።
የሥራ ኀላፊዎቹ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘውን ጨምሮ የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በአጼ ቴወድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዘጋቢ: ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!