ማኅበረሰቡ ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ።

27

ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በካናዳ የሥራ እና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ሕጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ(ዶ.ር) የተሰጣቸው በማስመሰል ሕገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚድያ አውታሮች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መኾኑንም ገልጿል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው እንዲህ አይነቱን የወንጀል ተግባር እየፈጸሙ የሚገኙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሠራ መኾኑ ተመላክቷል።

ኅብረተሰቡም ይህን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየንግዱ ማኅበረሰብ ለከተማዋ ልማት እና ሰላም የድርሻውን እንዲወጣ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ጠየቀ።
Next articleበአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።