
ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም የአማራ ብረታ ብረት ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ዘለዓለም በላይ በባሕርዳር ማቅለጫ ኢንዱስትሪ፣ በማሽነሪ -ኢንዱስትሪ እና በፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በሚገኙ አውቶሜትድ ሲ.ኤን.ሲ ማሽኖች እየተመረቱ የሚገኙ ስማርት ፖል እና ሌሎች ሥራዎችን አመራረት ሂደት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ ኩባንያቸው የዲጂታል ኢትዮጵያን ትራንስፎርሜሽን ከማፋጠን ጎን ለጎን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ሀገራዊ አቅምን ለማሳደግ ለሚደረገው ጥረት ከኢንዱስትሪው ጋር በስማርት ማኑፋክቸሪንግ፣ ስማርት ፖል ኢ.አር ፒ.እና ሌሎች ዲጂታል ሥራዎችን በጋራ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!