“የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ኹኔታችን ባለን አቅም የሚወሰን ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

27

ባሕርዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ኹኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተና እና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ባደረግነው ጉብኝት በርዕደ መሬት ነክ ሳይንሳዊ ምርምር አበረታች ሥራዎችን አይተናል ነው ያሉት።

ባለፈው ሳምንት ባካሄድነው የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በርዕደ መሬት ክስተት ዙሪያ ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሠረት ወደ ተጠናከረ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመሠረተ ልማት፣ የጊዜያዊ መጠለያ፣ የሰብአዊ ድጋፍ፣ የሳይንሳዊ ትንተና እና ትንበያ ቡድኖችን በማደራጀት በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ሥራ እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል።

መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት የጥናትና ምርምር ተቋማት ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ኃይል ጠንካራ ቁመና እንዲፈጥሩ ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአምስት የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ገለጸ።
Next articleየጥምቀት በዓል የወልድያ ከተማ ሃይማኖታዊ እና ማኅበራዊ ክዋኔ መገለጫ ነው።