
ባሕር ዳር: ጥር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ለ2017/18 የምርት ዘመን 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ገልጿል፡፡ ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ 206 ሺህ 267 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሲኾን 106 ሺህ 992 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን ወደብ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
ወደብ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ተሽከርካሪዎችን እና ባቡርን በመጠቀም በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ መኾኑም ተገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት 27 ሺህ 930 ሜትሪክ ቶን በባቡር እንዲሁም 178 ሺህ 314 ሜትሪክ ቶን በከባድ ተሽከርካሪዎች ከ150 በላይ ወደኾኑ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች መጓጓዙ ተጠቅሷል፡፡
እያንዳንዳቸው 60 ሺህ እና 56 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት ተጨማሪ መርከቦች በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ጅቡቲ እንደሚደርሱም ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!