የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ዲጅታላይዝድ አሠራርን መተግበር አስፈላጊ መኾኑን አቶ ዓለምአንተ አግደው ገለጹ።

35

ጎንደር: ጥር 07/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ፣ የዲጅታላይዝድ አሠራር እና የሰው ኃይል ግንባታን በተመለከተ በጎንደር ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል እና የዜጎችን ፍትሕ ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዘመኑን የሚመጥን ፍትሕ ለዜጎች ለመሥጠት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት እየሠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል።የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ዲጅታላይዝድ አሠራርን መተግበር አስፈላጊ መኾኑንም አመላክተዋል።

የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ከአጋር አካላት ጋር በመሥራት ፣ ውይይቶችን በማድረግ ጥንካሬውን ለማስቀጠል እና ድክመቶችን ለማረም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በውይይቱ የጎንደር ከተማ እና የዞን የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” ኪነ ጥበብ ሰላምን ለመገንባት መንገድ ኾኖ የቆየ ነው” አቶ ደሳለኝ ጣሰው
Next article“የዚህ ዘመን መሪዎች ሰላም እና ፍቅርን በመስበክ አርዓያ ኾነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል” መምህር ለዓለም ብርሃኑ