የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው በለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም ዙሪያ ለመምከር ጎንደር ተገኝተዋል።

43

ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ከማዕከላዊ ጎንደር እና በአካባቢው ካሉ ሌሎች ዞኖች እና የወረዳ ፍርድ ቤቶች ጋር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጀመራቸው ሁሉ አቀፍ የለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም ዙሪያ ለመምከር ነው ወደ ጎንደር ያቀኑት።

ፕሬዚዳንቱ እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ፣ ከሰሜን ጎንደር እና ከምዕራብ ጎንደር ዞኖች ከፍተኛ እና ወረዳ ፍርድ ቤቶች፣ እንዲሁም ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት ጋር ምክክር እና ዉይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጀመራቸው የትራንስፎርሜሽን፣ ዲጅታላይዜሽን፣ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት ትብብር ላይ በታቀዱ እና በተከናወኑ ጉዳዮች ላይ ከዞን እና ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች፣ ዳኞች እና ባለሙያዎች ጋር ምክክር የሚያደርጉ ሲሆን፣ ከዞን እና ወረዳ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች በዳኝነት እና በፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከሚሠሩ ባለድርሻዎች ጋርም የሚወያዩ ይሆናል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሬሕይዎት ታምሩ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
Next article“መንግሥት ነዳጅ ከዓለም ዋጋ እና ከጎረቤት ሀገራትም ዋጋ በታች በከፍተኛ ድጎማ እያቀረበ ነው” የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ