“የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅ ያስቻሉ ስኬታማ የዲኘሎማሲ ሥራዎች ተከናውነዋል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

20

ባሕርዳር: 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2017ዓ.ም የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሟል። በውይይቱ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ጂኦፓለቲካዊ ተግዳሮቶችን በማለፍ ዲኘሎማሲዊ ስኬቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ዲኘሎማሲ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅ ያስቻሉ ስኬታማ የዲኘሎማሲ ሥራዎች መከናወናቸው ተመላክቷል።

የባሕር በር ጉዳይን አጀንዳ በማድረግ የኢትዮጵያን ፍትሐዊ ፍላጎት እና ብሔራዊ ጥቅም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ ማድረግ ተችሏል ነው የተባለው። ኢትዮጵያ መልካም ጉርብትና እና ሁለንተናዊ ግንኙነትን ከጎረቤት ሀገራት ጋር እንድታሳድግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውም ተመላክቷል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት በአባልነት መመረጧ ባለፉት ስድሰት ወራት ከተገኙ ስኬቶች አንዱ መኾኑ ተጠቅሷል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሃብት በማፍራት እና ሙያን መሠረት ያደረገ የሰው ኃይል ስምሪት በማድረግ የተሻለ ሥራ መሥራቱም ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ.ር) እየተተገበሩ የሚገኙ የተቋሙን የለውጥ ሥራዎች በመፈተሽ በቀጣይ ስድስት ወራት በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። ሚስቴር መሥሪያ ቤቱን ዲጂታላይዝ ማድረግ እና የሥራ ከባቢን ማዘመን ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መኾናቸውን ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምሰጋኑ አርጋ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተመዘገቡ ዲኘሎማሲያዊ ስኬቶች በበርካታ ጂኦፓለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ በማለፍ የተገኙ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሰው ኃይል ሥልጠና ፣ በጥናትና ምርምር ፣ በወቅታዊ እና ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ የተሠሩ ሥራዎች አበረታች መኾናቸውም ተመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ.ር) የኖርዌይ ፍትሕ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸልን በጽሕፈት ቤታቸው አነጋነሩ።
Next articleየኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሬሕይዎት ታምሩ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።