
ባሕር ዳር: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ( ዶ.ር) ኖርዌይ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ከኾኑ ሀገራት መካከል አንዷ መኾኗን ገልጸዋል ።
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ የምትገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ኩባንያዎች የተሻለ የተሳትፎ ዕድልን የፈጠረ በመኾኑ የኖርዌይ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የኖርዌይ ፍትሕ ሚኒስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንነኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መኾኗን ተናገረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!