የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቅቆ ተመረቀ ፡፡

14

ባሕር ዳር: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ታሪካዊው እና ጥንታዊው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቅቆ ተመርቋል፡፡ የምረቃ መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አሥኪያጅ፣ የባሕርዳር እና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ኀላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክን ጨምሮ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኀላፊዎች እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍል ኀላፊዎች፣ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንዲሁም አማኞች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
Next article“የባሕል እና የኪነጥበብ ፌስቲቫሉ ለመቀራረብ እና ለመግባባት የማይተካ ሚና አለው” መልካሙ ጸጋዬ