
ባሕር ዳር: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ኢትዮ ቴሌኮም በትብብር በመሥራት ለዜጎች ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ናቸው።
ስምምነቱ በአማራ ክልል የሚገኙ ሁሉንም ፍርድ ቤቶች በኔትወርክ በማስተሳሰር ዜጎች ባሉበት አካባቢ ኾነው ዲጂታል አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ዲጂታል አገልግሎቱ የፍርድ ሥርዓቱን እንደሚያቀላጥፍ፣ የዜጎችን ጊዜ እና ኢኮኖሚ እንደሚቆጥብ ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!