የዘንድሮውን የተፈጥሮ ሃብት ሥራ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሠራ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታወቀ።

26

ገንዳ ውኃ: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የ2017 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ለመሥራት የዞን፣ የከተማ እና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ አንዳርጌ ጌጡ እንደገለጹት የሰው ልጅ ተፈጥሮን ተንከባክቦ መያዝ ከቻለ ተፈጥሮ ያለ ስስት ፀጋዋን ትሠጣለች ነው ያሉት።

የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የአንድ ሰው ሥራ ብቻ ሳይኾን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ጭምር ነው። በበጀት ዓመቱ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎችን ለማከናወን ከ33 ሺህ 500 በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሏል። የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅ ሥነ ምህዳሩን በማስተካከል የምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እያሱ ይላቅ የተፈጥሮ ሃብት ሥራዎችን በተገቢው መንገድ በመሥራት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ነጻ መኾን አለብን ብለዋል። አሁን ላይ ማኅበረሰቡ ያለበት ወቅታዊ ሥራ የቀነሰ በመኾኑ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራዎችን ለማከናወን አመች መኾኑንም ተናግረዋል።

ሁሉም በየድርሻው ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም እንዲሠራም አስገንዝበዋል። የመተማ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ደሳለኝ ሞገስ ሰላምን ከማጠናከር ጎን ለጎን የዘንድሮውን የተፈጥሮ ሃብት ሥራ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአቢሲኒያ ባንክ ለዕድለኞች ሽልማቶችን አስረከበ።
Next articleየደረሠኙ ክርክር